ቤት (ፊደል)
From Wikipedia, the free encyclopedia
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ
ቤት በአቡጊዳ ተራ ሁለተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያና በዓረብኛ ፊደሎች ሁለተኛው ፊደል «ቤት» ይባላል። በግሪክም ሁለተኛው ፊደል «ቤታ» ይባላል።
በቋንቋ ጥናት የዚሁ ድምፅ ፍች «ነዛሪ የከናፍር ፈንጂ» ይባላል።[1] በዕብራይስጥ አንድ ነጥብ በመሃል ውስጥ ሲኖር (בּ) ድምጹ እንደ «ብ» ቢመስልም ያለዚያ ነጥብ ግን (ב) እንደ «ቭ» ይሰማል። ለዚያም ደግሞ በአማርኛ ይህ ድምጽ «ቨ ቩ ቪ ቫ ቬ ቭ ቮ» በተለይ በባዕድ ቃላት ሲጋጠም ከ«በ...» ትንሽ ተቀይሯል።