ቦይንግ 787 ድሪምላይነር
From Wikipedia, the free encyclopedia
ቦይንግ 787 ድሪምላይነር በቦይንግ የተሠራ የረዥም ርቀት፣ ጥንድ ሞተር አውሮፕላን ነው። የአውሮፕላኑ አብዛኛው ክፍሎች ከካርቦን ኮምፖሲት ማቴሪያል በመሠራታቸው፣ አውሮፕላኑ ከቀደምት አውሮፕላኖች የቀለለ ነው።[1] የነዳጅ ፍጆታው ከሌሎች አውሮፕላኖች በ20 ከመቶ የተሻለ ሲሆን ፍጥነቱ ከድምፅ ፍጥነት በ11 ከመቶ ያንሳል።[1] ጃፓን ከዓለም የመጀመሪያው የድሪምላይነር አብራሪ ናት። ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ብቸኛዋ አብራሪ ናት።[1] የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጠቅላላ አሥር ድሪምላይነሮችን በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ገዝቷል።[1] ከተገዙት አሥር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቅባበል ተደርጎለታል።[2]