ኦይለር ቁጥር
From Wikipedia, the free encyclopedia
የኦይለር ቁጥር በእንግሊዝኛ e የሚል ምልክት ያለው ለሒሳብ ጥናት አስተዋጾ እያደረገ የሚገኝ ለየት ያለ ቁጥር ነው። ቁጥሩ በ2 እና በ3 መካከል የሚገኝ ሲሆን ዋጋውም ከሞላ ጎደል 2.71828.. ነው። የቁጥሩ ስም የመጣው ከስዊዘርላንዱ ሂሳብ ተመራማሪ ላዩናርድ ኦይለር (Leonhard Euler) ነው።
e ከሌሎች ቁጥሮች ለየት የሚልበት ምክንያት ይህን ቁጥር በ x ከፍ ስናረገው፣ f(x) = ex፣ የሚያስገኘው ዳገት ኩርባ (slope) x ባዶ ሲሆን አንድ ነው። ይህንንም በሰተቀኝ ከሚታየው የመለኪያ ሰንጠረዥ መረዳት ይቻላል። ባጠቃላይ መልኩ የf(x) ኩርባ ማንኛውም ቦታ ላይ ከf(x) ጋር አንድ ነው።