ደብረ ታቦር (ከተማ)
From Wikipedia, the free encyclopedia
ደብረ ታቦር (በሌላ ስሟ ጁራ ) በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ከጣና ሓይቅ ሰሜናዊ ምስራቅ 50 ኪሎ ሜተር ርቃ የምተገኝ በተራሮች የተከበበች ከተማ ናት። በከተማይቱ ዙሪያ 48 ምንጮች መኖራቸው ለከተማይቱ እድገት ከፍትኛ አስተዋጾ ቢያደርጉም በ20ኛው ክፍለ ዘመን የባህር ዛፍ ተክል በከተማይቱ መሰራጨት ምንጮቹ እንዲደርቁ አድርጓል። የደብረታቦርን መሰረት የጣለው የ14ኛ ክፍለዘመን ንጉስ አጼ ሰይፈ አርድ (1327-1372) ነበር። በዚህ ንጉስ ዘመን የታቦር እየሱስ ቤ/ክርስቲያን በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ታነጸ።[1] ራሱና ልጆቹ ለከተማይቱ መቋቋም አስተዋጾ ቢያበረክቱም ከተማይቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በሰፊው የምትጠቀሰው አጼ ቴወድሮስ እና ከዚያም ቀጥሎ አጼ ዮሐንስ ፬ኛ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በማገልገል ነው። ከዚያም በዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ ታላቁን እና ገናናውን ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንቁ ተደርጎ ተመስርቷል አሁንም ድረስ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና ነው ። ዛሬ ከተማይቱ ስትነሳ ደብረ ታቦር ኢየሱስን የማያስብ ለጉብኝት የመጣም ሳይጎበኘው መሄድ አይታሰብም ። ደብረ ታቦር(ጁራ) የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች። ተጭነው ስለተለያዩ የከተማይቱ ክፍሎች መርጃ የሚያገኙበት ካርታ እዚህ ይገኛል።
ደብረ ታቦር | |
በአጼ ቴወድሮስ እጅ የተሰራው ታቦር መድሃኔ አለም ቤ/ክርስቲያን | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | አማራ ክልል |
ዞን | ደቡብ ጎንደር |
ከፍታ | 2,706 |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 39,052 |