ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዳግማዊ ኢያሱ (ጥቅምት 21፣ 1723 እ.ኤ.አ - ሐምሌ 27፣ 1755) በዙፋን ስማቸው ዓለም ሰገድ ከመስከረም 19፣ 1730 ጀምሮ እስከ እለተ ህልፈታቸው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ሲሆን አባታቸው አጼ በካፋ ሲሆኑ እናታቸው እቴጌ ምንትዋብ (የክርስትና ስም - ወለተ ጊዮርጊስ) ነበሩ።[1]
==
Quick Facts ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ, ግዛት ...
ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ | |
---|---|
የዳግማዊ እያሱ አጽም ከእናቱ እቴጌ ምንትዋብና ልጁ ኢዮዋስ አጠገብ፣ ቁስቋም፣ ጎንደር | |
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ | |
ግዛት | ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፯፻፮ እስከ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፲፯፵፰ ዓ.ም. |
ቀዳሚ | በካፋ |
ተከታይ | ኢዮአስ |
ሙሉ ስም | ዓለም ሰገድ (የዙፋን ስም) |
ሥርወ-መንግሥት | ሰሎሞን |
አባት | በካፋ |
እናት | ምንትዋብ |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና |
Close
==
የወደፊቱ ዳግማዊ እያሱ ወደ ስልጣን በወጣበት ጊዜ ገና ህጻን ስለነበር እናቱ እቴጌ ምንትዋብ የልጁ እንደራሴ ሆና ተሾመች። ነገር ግን የልጁን መንገስ የሚፎካከሩ አካሎች የፋሲል ግቢን በመክበብ ጥቃት ማድረስ ጀመሩ። ስለሆነም ከጎጃም 30፣000 ሰራዊት ተነስቶ ጎንደር ስለገባ የስልጣን ተፎካካሪወች የፋሲልን ግቢ ጥሰው ውስጥ ሳይደርሱ ተሸነፉ.[2]። በዚህ ግርግር ምክንያት እቴጌ ምንትዋብ በእንደራሴነት ሳትወሰን እራሷ ላይ ዘውድ በመጫን ከልጇ ጋር እኩል ስልጣን እንዳላት አወጀች። በዚህ ሁኔታ የንግስትነት ማዕረግን ስትይዝ እቴጌ ምንትዋብ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ለመሆን በቃች።