ፒያኖ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፒያኖ በቁልፎች ድርድር ለመጫወት የሚያስችል ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያ ነው። ይህ መሣሪያ በአለማችን ላይ እጅግ የተለመደ ሲሆን በተለይም በሙዚቃ መሣሪያ ብቻ ለተቀናበሩ ሙዚቃዎች መስሪያነት ያገለግላል። በቀላሉ ለመያዝ የማይመች እና ዋጋውም እጅግ በጣም ውድ በመሆኑ በቀላል የሙዚቃ ቡድኖች ውስጥ አይገኝም። በዚህም ለከፍተኛ የሙዚቃ ቅንብሮች እና ትዕይንቶች ዋናውን ሚና የሚጫወት መሣሪያ ነው። በፒያኖ ላይ አንድን ቁልፍ መጫን ከበስተኋላው ያለው ወካይ መዶሻ ከብረት ተሠርተው የተወጠሩትን ጅማቶች እንዲመታ እና ድምፅ እንዲፈጥር ያደርገዋል።