ሥላሴ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሥላሴ ማለት ሠለሰ ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፣ ቃሉም የግእዝ ነው። ይህ ቃል የአምላክን አንድነትና ሦስትነትን ያመለክታል። የሥላሴ እምነት የክርስትና ሃይማኖቶች ተከታይ አንዷ ከሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዋነኛ መሰረተ ትምህርት ነው።
Quick Facts አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ, ሥሉስ ቅዱስ ...
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ | |
---|---|
ሥሉስ ቅዱስ | |
አነዋወር |
የነበሩ ያሉ ለሁልጊዜ የሚኖሩ ፣ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት በባሕርዪ አንድ የሆነ አምላክ ለቀዳማዊነቱ መጀመሪያ የሌለው ለደኃራዊነቱ መጨረሻ የሌለው አምላክ ወይም ትናንት የሌለበት ቀዳማዊ ዛሬ የሌለበት ማዕከላዊ ነገ የሌለበት ደኃራዊ አምላክ |
፩ኛ ዋና የአምላክ ትዕዛዝ ለሰው ልጅ | አምላክህን በሙሉ ልብህ በሙሉ ሀሳብህ በሙሉ ሰውነትህ በሙሉ ስሜትህ ውደድ |
፪ኛ ዋና የአምላክ ትዕዛዝ ለሰው ልጅ | ሌላውን ሰው እንደ ራስህ ውደድ |
የመጀመሪያ ክስተት ፩ኛ የንግሥ በዓል | ሐምሌ ፯ |
፪ኛው ዓመታዊ የንግሥ በዓል | ጥር ፯ |
Close
ትምህርቱ በዐቢይ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ (ተዋሕዶ፣ ምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት) ዘንድ ተቀባይ ሲሆን ማለትም በእንግሊዘኛ ሞኖቴዪዝም (Monotheism= በአንድ አምላክ ማመን) ይባላል፣ የሥላሴን አንድነት ያልተረዱ ወይም መረዳት የማይፈልጉ ፖሊቴዪዝም (በብዙ አምላክ ማመን= Polytheism) ብለው ይሰይሙታል ፣ ደግሞ ከማያስተምሩት ክፍልፋዮች መካከል አሪያኒስም፣ የይሖዋ ምስክሮች፣ እና ሞርሞኒስም ተገኝተዋል።