ሩሲያ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሩሲያ (መስኮብኛ፦ Россия /ሮሲያ/) ወይም የሩሲያ ፌዴሬሽን (መስኮብኛ፦ Российская Федерация /ሮሲስካያ ፍየድየራትሲያ/) በአውሮፓ እና እስያ አህጉሮች ውስጥ የምትገኝ አገር ናት። በ17,075,200 ካሬ ኪ.ሜ. ከዓለም በመሬት ስፋት አንደኛ ስትሆን በሕዝብ ብዛትም ከዓለም ስምንተኛ ናት። ሩስያ ከኖርዌ፣ ፊንላንድ፣ ኤስቶኒያ፣ ሌትላንድ (ላቲቪያ)፣ ሊትዌኒያ፣ ፖላንድ፣ ቤላሩስ፣ ዩክሬን፣ ጆርጂያ፣ አዘርባይጃን፣ ካዛኪስታን፣ የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ፣ ሞንጎሊያ እና ሰሜን ኮሪያ ጋር ድንበር አላት። ሞስኮ ዋና እና ትልቅ ከተማዋ ሲሆን ሴንት ፒተርስበርግ ሁለተኛው ትልቅ ከተማ ናት
የሩሲያ ፌዴሬሽን |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Госуда́рственный гимн Росси́йской Федера́ции |
||||||
ዋና ከተማ | ሞስኮ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ሩሲያኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ፕሬዚዳንታዊ ሪፐብሊክ ቭላዲሚር ፑቲን ሚክሄል ሚሹስቲን |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
17,075,400 (1ኛ) 13 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2017 እ.ኤ.አ. ግምት |
144,463,451 (9ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ሩብል | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +2 እስከ +11 | |||||
የስልክ መግቢያ | +7 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .ru .su .рф |
በምስራቃዊ አውሮፓ ክፍል የሚኖሩ የስላቭ ህብረተሰብ ወደ አሁኗ ሩስያ ከሶስት እስከ ስምንተኛው ክፍል ዘመን ተሰደዱ። ኬይቫን ረስ የሩስያ ህዝብ ማንነት እንዲኖሮ በማድረግ ከ9ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበረ ትልቅ ግዛት ነው። በተጨማሪም፣ የሩስያ ኦርቶዶክስ መነሳት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በ988 ዓም፣ ክርስትና ከቢዛንታይ ወደ ሩስያ ተስፋፋ። ልክ የረስ ስልጣን በሞንጎል ወረራ ሲዳከም፣ ምስራቃዊ ክፍሏ በልዕልና እስከ 13ተኛው ክፍለ ዘመን ይመራ ነበር። እስከ 18ተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ፣ ምዕራባዊው ግዛት በፍጥነት ድንበሯን ወደ ምስራቅ በማስፋፋት የሩስያ ኢምፓየር መመረት ችላለች። በ1917 የተነሳው የሩስያ አብዮት የመንግስቱን ስርአት ወደ ሶሻሊስት በመቀየር የሶቬት ህብረትን በ1922 አቋቋመች። ሰፊውን የምስራቃዊ አውሮፓና መካከለኛ እስያ ክፍልን የሚይዘው የሶቬት ህብረት በሁለተኛው የአለም ጦርነት አክሲስ ሀያላንን በመዋጋት ጎልህ ሚና ነበራት። ነገር ግን ከጆሴፍ ስታንሊን አመራር ጀምሮ፣ የሶቬት ህብረት አምባገነናዊ እየሆነ ሄደ። ብዙ ቤት ክርስቲያኖች ወደሙ፣ ብዙ ሰዎች ተገደሉ፣ ብዙ አይሁዶች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። የሶቬት ህብረት ከአሜሪካ ጋር የቀዝቃዛውን ጦርነት ስታስጀምር ብዙ ደባና ጭካኔ አድርሳለች። ለምሳሌ፣ የቬትናም ጦርነት ላይ ከአሜሪካ ጋር የውክልና ጦርነት በማድረግ ሰብዕዊ መብት ጥሳለች። በተቃራኒው ሶቬት በሳይንስና ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም መበልፀግ የጀመረችበት ጊዜ ነበር። በማርክሲዝ ሌኒንዝም አብዮት የተሞላችው ሶቬት ህብረት በ1991 በህዝበ ውሳኔ ልትፈርስ ችላለች። ሩስያ በ1993 መንግስቷን ወደ ፌድራል ልትቀይር ችላለች፤ እስካሁንም ትመራለች።
ሩስያ ሀያላን ሀገር ናት። በተጨማሪም በጦርና በማዕድን የምትታወቅ ናት።