ዓፄ ሱሰኒዮስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዓፄ ሱስኒዩስ በዙፋን ስማቸው "መልአክ ሰገድ" ተብለው ሲታወቁ በ1572 ተወልደው በ1632 (እ.ኤ.አ)አርፈዋል። ከ1606–1632 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ሲሆን፣ አባታቸው የአፄ ልብነ ድንግል የልጅ ልጅ የሆኑት አቤቶ ፋሲለደስ እና ልጃቸው ደግሞ ዓፄ ፋሲለደስ ነበሩ። እናታቸው ወይዘሮ ሐመልማለ-ወርቅ የተሰኙ የጎጃም አስተዳዳሪ ልጅ ነበሩ።
==
Quick Facts ዓፄ ሱስኒዮስ, ግዛት ...
ዓፄ ሱስኒዮስ | |
---|---|
ማሪያም ግምብ የአፄ ሱስኒዮስ ቤተ መንግስት በጎርጎራ | |
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ | |
ግዛት | ከ1606 እስከ 1632 እ.ኤ.አ. |
በዓለ ንግሥ | 1608 እ.ኤ.አ. |
ቀዳሚ | ዓፄ ያዕቆብ |
ተከታይ | አፄ ፋሲለደስ |
ልጆች | አፄ ፋሲለደስ |
ሙሉ ስም | መልአክ ሰገድ (የዙፋን ስም) |
ሥርወ-መንግሥት | ሰሎሞን |
አባት | አቤቶ ፋሲለደስ |
እናት | ወ/ሮ ሐመልማለ-ወርቅ |
የተወለዱት | 1572 እ.ኤ.አ. |
የሞቱት | 1632 እ.ኤ.አ. |
ሀይማኖት | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ ከ1622 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ የሮማ ካቶሊክ ክርስትና |
Close
==
በሱሰንዮስ ዘመን የነበረው የጀስዩት ሚስዩን አልሜዳ ሱሰንዩስ "ረጅም፣ ወንዳወንድ፣ ትላልቅ አይኖች ያሉት፣ አፍንጫው ቀጥ ያለና ጢሙም በጥንቃቄ የተከረከመ ነው" ካለ በኋላ አለባበሱን ሲገልፅ " [በጊዜው የአውሮጳውያን ፋሽን የነበረውን አይነት] እስከ ጉልበቱ የሚደርስ ከደማቅ ቀይ ሐር የተሰራ በፍታ በስስ ጥብቅ ያለ ሱሪ እና በትላልቅ ወርቅ ያጌጠ ቀበቶ ለብሶ ከላዩ ላይ በተለያየ ቅርጻቅርጽ ያጌጠ ካባ ይደርባል። "[1]