ሚካኤል
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሚካኤል (በዕብራይስጥ: מִיכָאֵל, ሲነበብ፡ ሚካኤል, ሲተረጎም፡ 'ማንነው እንደ እግዚአብሔር?'; በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl; በላቲን: Michahel-ሲነበብ፡ ሚካኤል; በአረቢኛ: ميخائيل, ሲነበብ፡ ሚካኤል) በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላዕክት ተብሎ ይጠራል
ቅዱስ ሚካኤል | |
---|---|
ሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል | |
መዐረግ |
የስድስቱ ሊቃነመላዕክት አለቃ ፩ኛ ቅዱስ ገብርኤል ፪ኛ ቅዱስ ሩፋኤል ፫ኛ ቅዱስ ራጉኤል ፬ኛ ቅዱስ ፋኑኤል ፭ኛ ቅዱስ ዑራኤል ፮ኛ ቅዱስ አፍኒን እንዲሁም የ፺፱ ነገደ መላእክት |
፩ኛ በዓለ ንግሥ | ኅዳር ፲፪ እስራኤላውያንን ቀይ ባሕርን ያሻገረበት |
፪ኛ በዓለ ንግሥ | ሰኔ ፲፪ የባሕራምን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት |
ሚካኤል ማለት | ዕፁብ ድንቅ ነገር |
መላእክት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
የቅዱስ ማካኤልን ድርሳን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ድርሳነ ሚካኤል
በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ይመለከቱ
ሰውን ይረዳሉ ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/
ስግደት ይገባቸዋል ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15