ቅዱስ ያሬድ
የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ካህንና የዜማና የድርሰት ሊቀ ሊቃውንት / From Wikipedia, the free encyclopedia
አባታችን ቅዱስ ያሬድ ሚያዝያ ፭ ቀን በ፭፻፭ ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ፡፡ አባቱ አብዩድ ወይም ይስሐቅ ይባላል እናቱ ክሪስቲና ወይም ታውክልያ ትባላለች። ቅዱስ ያሬድ በተወለደ በ7 ዓመቱ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ገበዝ ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እንዲያሳድገውና እንዲያስተምረው አደራ ሰጠችው፡፡
Quick Facts ቅዱስ ያሬድ, ሊቀ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ...
ቅዱስ ያሬድ | |
---|---|
ሊቀ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ | |
ስም | ያሬድ |
የተወለደበት ቀን | ሚያዚያ ፭ ቀን ፭፻፭ ዓ.ም. |
የሚታወቅበት | ዜማን በፅሑፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቀናበረ |
የትውልድ ቦታ | አክሱም |
ንግሥ | ግንቦት ፲፩ |
የአባት ስም | ይሥአቅ (አብዩድ) |
የእናት ስም | ክሪስቲን(ተውኪልያ) |
ሥራው | የቤተክህነት ዜማ አቀናባሪ፣ደራሲ፣ፀሐፊ |
የሚከበረው |
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ አገሮች አስደናቂ ስጦታውን በሚያውቁት ዘንድ |
Close
ያሬድ ከአጎቱ ዘንድ መዝሙረ ዳዊት በሚማርበት ጊዜ ስለሚቆጣውና ስለሚገርፈው መታገስ ተስኖት ማይኪራህ ወደምትባል ቦታ ሄዶ ተደበቀ ያም ቦታ የቀዳማዊ ምኒልክ መቃብር ቦታ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ወደ አንዲት ዛፍ ስር ተጠግቶ አርፎ እያለ አንዲት ትል የዛፍ ፍሬ ለመብላት ዛፉ ላይ ለመውጣት ስድስት ጊዜ ሲወጣና ሲወርድ ከቆያ በኃላ በሰባተኛው ከዛፉ ላይ ወጥቶ የዛፉን ፍሬ ሲበላ ተመለከተ፡፡ ቅዱስ ያሬድ የትሉን ተስፋ አለመቁረጥ ከፍተኛ የሆነ ትጋቱን እንዲሁም ወደላይ ለመውጣት ብዙ ጊዜ እየሞከረ ቢወድቅም ከዓላማው ሳይናወጥ ከብዙ ድካምና ጥረት በኃላ ያሰበው እንደተፈጸመለት ተመልክቶ “ሰውነቴ ሆይ ግርፋትን ለምን አትታገሽም፤ መከራንስ ለምን አትቀበይም” ብሎ ሰውነቱን ከገሰጸ በኃላ ወደ መምህሩ ተመልሶ “አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝ እንደቀድሞ አስተምረኝ” አለው፡፡ መምህሩ ጌዴዋንም ተቀብሎ ያስተምረው ጀመር፡፡