ፍሬምናጦስ
የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ጳጳስ / From Wikipedia, the free encyclopedia
ፍሬምናጦስ በእንግሊዘኛ Frumentius የተወለዱት ታይር በምትባል ቦታ በምሥራቃዊ የሮማ ነገሥት በ፬ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎቹ ሲሆን ማንም መርምሮ ሊደርስበት በማይችለው በእግዚአብሔር ሀሳብ ወደ ኢትዮጵያ መተው ክርስትናን ከመሠረቱት ዋነኛው አባት ሆኖ በመቆጠር ፣ አገራችንን ከሌሎች ክርስቲያን አገሮች ጋር ያስተዋወቁ ፣ ያስተካከሉ ፣ በአክሱም ዘመነ መንግሥትና መንግሥት የተወደዱና የተከበሩ ፣ በመላው ኢትዮጵያ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የተከበሩ ታላቅ አባት ናቸው ።
Quick Facts ቅዱስ ፍሬምናጦስ, አቡነ ሰላማ ክሳቴ ብርሃን ...
ቅዱስ ፍሬምናጦስ | |
---|---|
አቡነ ሰላማ ክሳቴ ብርሃን | |
ስም | መጀመሪያ ፍሬምናጦስ በኋላ አቡነ ሰላማ ክሳቴ ብርሃን |
የተወለዱት | በ፬ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ |
የትውልድ ቦታ | ሶርያ |
ኖረው ያረፉት በአክሱም | በአክሱም ኢትዮጵያ በ፫፻፸፭ ዓ.ም. |
ዓመታዊ በዓላቸው የሚከበረው |
ታኅሣሥ ፲፰ ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዲሴምበር 14 በጁሊያን ካላንደር ኦክቶበር 27 በጌሬጎሪያን አቆጣጠር |
የሚከበሩት | |
Close
አባታችን ፍሬምናጦስ የ፲፪ ዓመት ልጅ እያለ ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ ፈላስፋም የነበረ መርከበኛ ይዞት ወደ አገራችን መጣ ። ከእርሱም ጋር ወንድሙ ኤድስዮስ የተባለም አብሮት እንደነበረ ይታወቃል ። እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ የመጣው ሜሮጵዮስ በቀይ ባሕር አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በጣሉለት አደጋ በዚሁ እንደ ሞተ ታሪክ ይነግረናል ። ይህም በንጉሥ ዒዛና ዘመነ መንግሥት ሆነ ።