መንዝ
From Wikipedia, the free encyclopedia
መንዝ የሚለው ስያሜ የመጣው ከግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙና አመጣጡም መንዛት መርጨት ከሚለው ቃል የመጣ ሲኾን ሊቀ መልዐክቱ ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም የረጨባት የምድር ማእከል ናት ፡፡
መንዝ ማለትም ደሙን የረጨበት ስለሆነ ነዝሃ መንዝ ተባለ ፡፡
ቅዱሱ ጽዋም እዚችው ምድር ሲገኝ ብዙ ምስጢራት ስላላት ከዚህ በላይ መናገር አልችለም ፡፡በጣምም ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡
መንዝ በሰሜናዊ ሸዋ የሚገኝ ክፍል ሲሆን በውስጡ ላሎ ምድርን በስተደቡብ፣ ጌራ ምድርን በስተሰሜንና ማማ ምድርን በመካከል ይዞ ይገኛል[1] ። የመንዝ ድንበር በ3 ወንዞችና በአንድ ተራራ እንዲህ ይካለላል፦ ሞፋር ወንዝ (ደቡብ)፣ አዳባይ ወንዝና ወንጭት ወንዝ (ምዕራብ)፣ ቀጨኔ ወንዝ (በሰሜን) እንዲሁም በስተምስራቅ ከቆላው ኤፍራታ፣ ግድምና ቀወት የሚለየው የተራራ ሰንሰለት ናቸው [2] ።