ማልኮም ኤክስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ማልኮም ኤክስ (Malcolm X 1917-1957 ዓም) በአሜሪካ አገር ታዋቂ የብሔራዊ መብቶች እንቅስቃሴ መሪ ነበር። ማልኮም ኤክስ (የትውልድ ስሙ ማልኮም ሊትል፣ በኋላ ኤል-ሀጅ ማሊክ ኤል-ሻባዝ፣ ግንቦት 19፣ 1925 የተወለደ - ፌብሩዋሪ 21፣ 1965 በሞት ተለየ) በሲቪል መብቶች ንቅናቄ ወቅት ታዋቂ ሰው የነበረ አሜሪካዊ የሙስሊም ሚሲዮን እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነበር። እ.ኤ.አ. እስከ 1964 ድረስ “የኔሽን ኦፍ ኢስላም ቃል አቀባይ”፣ የጥቁር አሜሪካውያን መብት ተሟጋች እና እስልምናን በአሜሪካ የጥቁር ማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት እንዲኖረው ከፍተኛ አስተዋጸኦ በማድረግ የሚታወቅ ሰው ነበር።
==
ማልኮም ኤክስ | |
---|---|
ማልኮም ኤክስ በ1964 ዓም | |
ባለቤት | ቤቲ ኤክስ |
ልጆች | 6 ልጆች አታላህ ሻባዝ ቃቢላ ሻባዝ ኢልያስ ሻባዝ |
ሙሉ ስም | ኤል-ሀጅ ማሊክ ኤል-ሻባዝ |
የተወለዱት | ኦማሃ ኔብራስካ፣ ሰሜን አሜሪካ |
የሞቱት | ኒው ዮርክ፣ ሰሜን አሜሪካ |
የተቀበሩት | ፌርን ክሊፍ የመቃብር ቦታ |
ፊርማ | |
ሀይማኖት | እስልምና |
==
በመጀመርያ በአንድ አነስተኛ ክፍልፋይ «ኔሽን ኦፍ ኢስላም» («የእስልምና ብሔር») ውስጥ አባል ሆነና የልደቱን ስም ማልኮም ሊተል የባርያ ፈንጋይ ቤተሠብ ስም ብሎት ወደ «ማልኮም ኤክስ» ቀየረው። ክፍልፋዩ «ኔሽን ኦፍ ኢስላም» ቢባልም፣ ትምህርቱ ግን እንደ እስልምና በፍጹም አይመስልም። መሪያቸው ስለ መሥራቹ አምልኮት ይሰብክ ነበርና ነጮች ሁሉ አጋንንት እንደ ነበሩ ያስተምር ነበር። ከጊዜ በኋላ ማልኮም ኤክስ ሀሣቡን ቀይሮ ከ«ኔሽን ኦፍ ኢስላም» ለቅቆ ወጣ፣ እምነቱም ወደ ሱኒ እስልምና ቀየረ። የሌሎችን ሰብአዊ መብት ለመከልከል ያሠበው ሁሉ ማናቸውም ዘር ቢሆን እሱ ጋኔኑ ነው ብሎ ያስተምር ጀመር። በዚህም ውቅት ወደ መካና ወደ አፍሪካም ጎብኞ ነበር።