ቤተ ማርያም
From Wikipedia, the free encyclopedia
ቤተ ማርያም በራሱ ሰፊ ግቢ የሚገኝ የላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቲያን ነው። ወደ ቤትክርስቲያኑ ለማለፍ በቤተ መድሃኒ አለም ምዕራብ በሚገኘው አጭር ዋሻ መንገድ ውስጥ ማለፍ ግድ ይላል። ቤተ ማርያም በአራቱም አቅጣጫ ቤተርክስቲያኖች ከበዋታል። በምስራቅ ቤተ መድኃኔ አለም፣ በምዕራብ ቤተ ጎልጎታ፣ በሰመን ቤተ መስቀል፣ እና በደቡብ ቤተ ደናግል ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ በቅዱስ ላሊበላ ከተገነቡት ሁሉ ቀደምት እንደንበረች ትውፊት አለ።
Quick Facts የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ቅርስ, ቤተ ማርያም ...
| ||||
---|---|---|---|---|
ቤተ ማርያም | ||||
ቤተ ማርያም | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ዓይነት | ባሕላዊ | |||
መመዘኛ | c(i)(ii)(iii) | |||
የውጭ ማጣቀሻ | 18 | |||
አካባቢ** | አፍሪካ | |||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርስ የሆነበት ጊዜ | 1970 (2ኛ ጉባኤ) | |||
* በዩ.ኔ.ስ.ኮ ስሙ እንደሰፈረ። ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
Close