አሞራ
From Wikipedia, the free encyclopedia
አሞራ መንገድ ጠራጊ ወፍ በተለይ የአውሬ በድን የሚበላ ነው። አሞራዎች በማናቸውም አህጉር ላይ ሲገኙ በአንታርክቲካ ወይም በፓሲፊክ ደሴቶች ላይ ግን አይገኙም።
ከአሞሮች ብዙዎቹ ከላባ መላጣ የሆነ ራስ ይኖራቸዋል። ምክንያቱ ባለ-ላባ ራስ በየጊዜ በደም ተቀብቶ ለማጽዳት ያስቸግረው እንደ ነበር ይመስላል። ከዚያ በላይ በወንዝ ውስጥ በቀላሉ ለማጽዳት ያስችለዋል።
አሞራዎች በ2 ክፍሎች ይገኛሉ። በአፍሪካ በእስያና በአውሮፓ የሚገኘው አሞራ ወገን ከጭላት፣ ንሥር፣ ጭልፊት፣ ጥምብ አንሣ ጋር በጭላት አስተኔ ውስጥ ይከተታል። በድን ለማግኘት የሚቻላቸው በማየት ብቻ ነው።
በአዲስ አለም (አሜሪካዎች) የሚገኙት አሞሮች ሌላ ወገን ናቸው። እነሱ መብል የሚያገኙ በማሽተት ነው።