አባል:Ewket Fana/ባለአንጓ ትሎች
From Wikipedia, the free encyclopedia
ባለአንጓ ትሎች / ˈænəlɪdz / ( አኔሊዳ / ə ˈ nëlɪdə / ፣ በላቲን አኔሉስ _ _ _ _ anellus _ ፣ “ትንሽ ቀለበት” ማለት ነው። [3] ) ፣እንዲሁም ባል ክፍልፍል ትሎች በመባል የሚታወቁ ሲሆን "ragworms"፣ የመሬት ትሎችን እና "leeches"ን ጨምሮ ከ22,000 በላይ አሁንም ያሉ ዝርያዎች በስሩ ያሉት ግዙፍ ክፍልስፍን ነው። ዝርያዎቹ በተለያዩ ስርአተ ምህዳሮች ውስጥ ተላምደው ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ማእበል እና ፍልውሃ ባለባቸው በባህር አካባቢዎች፣ ሌሎች በንጹህ ውሃ ውስጥ ፣ እና ሌሎች ደግሞ እርጥበት ባለው የየብስ አካባቢዎች ውስጥ ይገኛሉ።
ባለአንጓ ትሎች በሁለትዮሽ የተመጣጠነ ፣ ስሉስድርባዊ ፣ ወናአካላዊ ፣ ኢደንደሴ ዘአካላት ናቸው። ለእንቀስቃሴ ደግሞ ፓራፖዲያም አላቸው። አብዛኛዎቹ የመማሪያ መፃህፍት አሁንም ባህላዊውን ክፍፍል ወደ ፖሊቼቶች (ሁሉም የባህር ውስጥ ማለት ይቻላል)፣ ኦሊጎቼትስ (የምድር ትሎችን የሚያጠቃልሉ) እና ሊች -መሰል ዝርያዎችን ይጠቀማሉ። እ.ኤ.አ. ከ1997 ጀምሮ ክላዲስቲካዊ ምርምር ይህንን እቅድ በከፍተኛ ደረጃ ቀይሮታል፣ ሊችን እንደ ኦሊጎቼቶች ንዑስ ቡድን እና ኦሊጎቼቶችን ደግሞ እንደ ፖሊቼቶች ንዑስ ቡድን በመመልከት። በተጨማሪም ፖጎኖፎራ, ኢቺዩራ እና ሲፑንኩላ, ቀደም ሲል እንደ የተለዩ ክፍለስፍን ተደርገው ይታዩ የነበሩት፣ አሁን እንደ የፖሊቼቶች ንዑስ ቡድኖች ተደርገው ይቆጠራሉ። ባለአንጓ ትሎች የፕሮቶስቶምስ ዛጎል ለበሶችን ፣ ብራቺዮፖዶችን እና ኔመርቴያዎች የሚያጠቃልለውየሎፎትሮኮዞኣ አባላት ተደርገው ይወሰዳሉ።
የመሠረታዊ የባለአንጓ ትሎች ቅርጽ ብዙ አንጓዎችን ያካትታል። እያንዳንዱ አንጓ አንድ አይነት የአካል ክፍሎች ይሉት እና በአብዛኛዎቹ ፖሊቼቶች ውስጥ ብዙ ዝርያዎች ለመንቀሳቀስ የሚጠቀሙባቸው ጥንድ ፓራፖዲያ አላቸው። ምክፈሎች የበርካታ ዝርያዎችን አንጓዎች ይለያሉ፣ ነገር ግን በሌሎች ውስጥ በደንብ አልተገለጹም ወይም የሉም፤ በኢኩሪያ እና በኦቾሎኒ ትሎች ምንም ግልጽ የመለያየት ምልክቶች አያሳዩም። በደንብ የዳበረ ምክፈል ባላቸው ዝርያዎች ውስጥ, ደሙ ሙሉ በሙሉ በደም ሥሮች ውስጥ ይሰራጫል፣ እና በእነዚህ ዝርያዎች ከፊት ለፊት ባሉት አንጓዎች ውስጥ ያሉት የደምስሮች ብዙውን ጊዜ እንደ ልብ በሚሠሩ ጡንቻዎች የተገነቡ ናቸው። የእንደዚህ ዓይነቶቹ ዝርያዎች ምክፈሎች የእያንዳንዱን አንጓ ቅርጽ በመቀያየር በሞገደ ትፊት(በሰውነት ውስጥ በሚያልፉ “ሞገዶች”) አማካኝነት እንቅስቃሴን ለማሳለጥ ወይም ከፍና ዝቅ እያሉ የፓራፖዲያን ውጤታማነት ያሻሽላሉ። ምክፈሎች ባልተሟሉላቸው ወይም በሌሉአቸው ዝርያዎች ደሙ ምንም አይነት ፓምፕ ሳይኖር በዋናው የሰውነት ክፍተት ውስጥ ይሰራጫል። እና ብዙ አይነት የእንቅስቃሴ ስልቶች አሉ - አንዳንድ እራሳቸውን የሚቀብሩ ዝርያዎች ጉሮሯቸውን በመገልበጥ እራሳቸውን በደለል ውስጥ ይጎትታሉ።
የምድር ትሎች እንደ ታዳኝ በመሆንም ሆነ በአንዳንድ ክልሎች አፈርን በማበልጸግ እና አየር በመስጠት በምድር ላይ ያሉ የምግብ ሰንሰለቶችን የሚደግፉ ኦሊጎቼቶች ናቸው። በባህር ዳርቻ አካባቢ ከሚገኙት የሁሉም ዝርያዎች አንድ ሶስተኛውን ሊይዝ የሚችሉት እራሳቸውን የሚቀብሩ የባህር ፖሊቼቶች ውሃ እና ኦክሲጅን ወደ ባህር ወለል ውስጥ ዘልቀው እንዲገቡ በማድረግ የስነ-ምህዳር እድገትን ይደግፋሉ። ባለአንጓ ትሎች የአፈርን ለምነት ከማሻሻል በተጨማሪ ሰዎችን እንደ ምግብነትና ማጥመጃነት ያገለግላሉ። የሳይንስ ሊቃውንት የባህር እና የለጋ ውሃ ጥራትን ለመከታተል ባለአንጓ ትሎችን ይመለከታሉ። ምንም እንኳን የተበከል ደምን ማስወገድ በዶክተሮች ከቀድሞው በቀነሰ መልኩ ጥቅም ላይ የሚውል ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት ምዕተ ዓመታት ውስጥ ለዚህ ዓላማ ከመጠን በላይ በመሰብሰብ ምክኒያት አንዳንድ የሊች ዝርያዎች ለመጥፋት የተቃረቡ ዝርያዎች ተደርገው ይወሰዳሉ። የራግዎርሞች መንጋጋዎች ለየት ባለመልኩ የጥንካሬ እና ቀላልነት ጥምረት ስለሚሰጡ አሁን በመሐንዲሶች እየተጠና ነው።
ባለአንጓ ትሎች ለስላሳ አካል ያላቸው በመሆኑ ቅሪተ አካላቸው እምብዛም አይገኙም በአብዛኛው መንጋጋ እና አንዳንድ ዝርያዎች ያወጡት በማዕድን የተሰሩ ቱቦዎች። ምንም እንኳን አንዳንድ ዘግይተው የነበሩት የኤዲካራን ቅሪተ አካላት ባለአንጓ ትሎችን ሊወክሉ ቢችሉም፣ በአስተማማኝ መልኩ የታወቀው እጅግ ጥንታዊው ቅሪተ አካል የመጣው ከ 518 ከሚሊዮን አመታት በፊት ቀደም ባለው የካምብሪያን ዘመን አካባቢ ነው። የአብዛኞቹ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ፖሊቼቶች ቡድኖች ቅሪተ አካላት የታዩት በካርቦኒፌረስ ዘመን መገባደጃ ላይ ከ299 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ነበር። የቅሪተ አካል ጥናት ባለሙያዎች ከኦርዶቪሻን ዘመን አጋማሽ ከ472 እስከ 461 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የሆኑ አንዳንድ የአካላት ቅሪቶች የኦሊጎቼቶች ቅሪት አካላት መሆናቸው እና አለመሆናቸው ላይ አይስማሙም። የመጀመሪያዎቹ የማያከራክሩ የቡድኑ ቅሪተ አካላት ከ66 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በጀመረው በፓሌኦጂን ዘመን ውስጥ ይታያሉ።[4]