ጥቅምት ፯
- ፲፱፻፳፬ ዓ.ም - በአሜሪካ ውስጥ፣ በተለይም ሺካጎ ከተማ የሚኖረው ወንበዴ አል ካፖን «የቀረጥ ወንጀል» በመፈጸም ተከሶ የ፲፩ ዓመት እሥራት ተፈረደበት።
- ፲፱፻፳፮ ዓ.ም - ታዋቂው አይሁዳዊው የጀርመን ጉስነኛ(physicist) አልበርት ኣይንስታይን በትውልድ አገሩ እየገነነ ከመጣው የናዚ ጭቆናና ሥርዐተ መንግሥት ሸሽቶ አሜሪካ አገር ገባ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሶርያን ሪፑብሊክ ሕጋዊነት እንደሚያውቅና እንደሚያከብር ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ.ም - አረባዊ የነዳጅ አምራች አገሮች፣ እስራኤልን ረድታችኋል በማለት የወነጀሏቸውን ምዕራባዊ አገሮችችና በጃፓን ላይ ለአንድ ዓመት ሙሉ የነዳጅ ክልከላ ስልት አካሄዱ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኅብረተ-ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት በመላ አገሪቱ የነበሩትን የማዘጋጃ ቤት ሸንጎዎች እንዲዘጉ አዘዘ።