ዘሃራ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዘሃራ ወይም ቬነስ፡ (ምልክት፦) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፕላኔት ከፀሐይ ባለው ርቀት ሁለተኛ ቅርቡ (2ኛው) ነው። ከበስተኋላው ሰባቱ ፈለኮች ማለትም መሬት፣ ማርስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ። ከፊቱ የምትገኘው ብቸኛዋ ፈለክ ኣጣርድ ናት።
ዘሃራ የሚለው ስም ከአረብኛ «ዙህራ» ሲሆን ይህ ማለት ቁንጅና ወይም አበባ ነው። በአንድ ጥንታዊ የአረብ ትውፊት ዘንድ ዙህራ የተባለች ሴት በተዓምር ፈለክ ሆነች። አረቦች ይህን ትውፊት ከአይሁዶች፣ አይሁዶችም ከባቢሎን ሰዎች እንደ በደሩት ይታመናል። በአረመኔ እምነቶች ፈለኩ በፍቅር ጣዖት ስም ይባል ነበር፤ በእንግሊዝኛ ቬነስ የሚለው ስም ከሮማይስጥ የጣዖት ስም ነው።
በእብራይስጥ ደግሞ ለዚሁ ፈለክ ያለው ስም «ኖጋህ» ሲሆን ይህ በአማርኛ ማለት «ንጋት» ነው (የንጋት ኮከብ)። በአፋን ኦሮሞ «በከልቸ» ይባላል። በሶማለኛ ደግሞ «ወሀርሂር» ይባላል።