ጥሩነሽ ዲባባ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጥሩነሽ ዲዲባባ በመስከረም 21 ቀን 1978 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በአርሲ ክፍለ ሀገር በቼፋ ወረዳ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት 3 ናት። የጥሩነሽ አስተዳደግ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው። ነገር ግን የጥሩነሽ ቤተሰቦች የረጅም ርቀት አትሌቶች ናቸው። አክስቷ ደራርቱ ቱሉ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ እና አንድ ጊዜ ደግሞ የ 10000 ሜትር አሸናፊ እና የብዙ አገር አቋራጭ ውድድር አሸናፊ ነበረች። ሌላ አክስቷም በቀሉ ዲባባ ጥሩ ሯጭ ነበረች ጥሩነሽ ልጅ እያለች በበቆጂ ስትኖር። ሌላዋ እህትዋ እጅጋየሁ ዲባባ ከጥሩነሽ ቀደም ብላ መሮጥ ጀምራ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የቤተሰብዋን ፈለግ መከተል የጀመረችው እድሜዋ ከፍ ካለ በኋላ ነው። ጥሩነሽ ዲባባ ከ ሯጭ ቤተሰብ ብትፈጠርም ለመሮጥ ግን ምንም ፍላጎት አልነበራትም። ቱሉ በባርሴሎና ኦሎምፒክ በ 10000 ሜትር ባሸነፈች በሰባት አመቱ ጥሩነሽ ወደ አዲስ አበባ በ 2000 ዓ/ም መንገድ ጀመረች። ነገር ግን በቀሉ ዲባባ አባል ከሆነችበት ከእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ቡድን ስፖርት መስሪያ ክበብ ውስጥ አስመዝግባት ልምምድ ቀጠለች። ጥሩነሽ ዲባባ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዷ ለመሆን በቃች። ጥሩነሽ ዲባባ በ 14 አመት እድሜዋ በጣም ወጣት እና ሰውነትዋም ተሰባሪ ይመስል ነበር። ብዙዎችም በሩጫ ምንም ተስፋ እንደሌላት እና ሩጫው የሚጠይቀውን ጠንካራ ሰውነት የላትም ብለው ያምኑ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የኢትዮጵያ የረጅም ርቀት ተወዳዳሪ አትሌት ናት። በ 5000ሜትር የአለም ክብረ ወስን ባለቤት ስትሆን በ5000 ሜትር እና በ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር አሸናፊ ናት። ጥሩነሽ አራት የአለም አቀፍ ውድድር እና አምስት የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፊ ናት። በቅጽል ስም “የሕጻን ፊት ያላት ደምሳሽ” በማለት ይጠሩዋታል።
የሜዳሊያ መዝገብ | ||
---|---|---|
ጥሩነሽ በ2008 እ.ኤ.አ. በተካሔደው ቢስሌት ጨዋታዎች. | ||
Women's Athletics | ||
ለ ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ | ||
Olympic Games | ||
ወርቅ | 2012 London | 10000 m |
ወርቅ | 2008 Beijing | 10000 m |
ወርቅ | 2008 Beijing | 5000 m |
ነሐስ | 2004 Athens | 5000 m |
World Championships | ||
ወርቅ | 2003 Paris | 5000 m |
ወርቅ | 2005 Helsinki | 5000 m |
ወርቅ | 2005 Helsinki | 10000 m |
ወርቅ | 2007 Osaka | 10000 m |
ወርቅ | 2013 Moscow | 10000 m |
World Cross Country Championships | ||
ወርቅ | 2003 Lausanne | Junior race |
ወርቅ | 2005 Saint-Galmier | Short race |
ወርቅ | 2005 Saint-Galmier | Long race |
ወርቅ | 2006 Fukuoka | Long race |
ወርቅ | 2008 Edinburgh | Senior race |
ብር | 2002 Dublin | Junior race |
ብር | 2004 Bruxelles | Short race |
ብር | 2007 Mombasa | Senior race |
African Championships | ||
ወርቅ | 2008 Addis Ababa | 10000 m |
ወርቅ | 2010 Nairobi | 10000 m |
ብር | 2006 Bambous | 5000 m |
World Junior Championships | ||
ብር | 2002 Kingston | 5000 m |