ፓይ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፓይ ወይም በተለምዶ አጻጻፉ π የሚታወቀው ቁጥር የማንኛውም ክብ መጠነ ዙሪያ ለወገብ ርዝመት (ዲያሜትሩ) ሲካፈል የሚገኘው ምንጊዜም የማይቀየረው ቋሚ ቁጥር ነው።
የፓይን እርግጠኛ ዋጋ ማወቅ ባይቻለም ከ 3.141593 እንደሚጠጋ ግን በሂሳብ ስሌት የተደረሰበት ጉዳይ ነው። የፈለግነውን ሁለት ሙሉ ቁጥሮች አካፍለን ፓይን ማግኘት ስለማንችል ኢራሽናል ቁጥር ነው ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ፓይ በነጥብ ስርዓት (decimal system) ሲጻፍ አሃዞቹ ወይም አያበቁም ወይም ደግሞ እራሳቸውን አይደግሙም ፣ ይልቁኑ በማያባራ ዘፈቀደ ሁኔታ ይነጉዳሉ። ይህን ጉዳይ እታች በበለጠ እናየዋለን።