ማርክሲስም-ሌኒኒስም
From Wikipedia, the free encyclopedia
ማርክሲስም-ሌኒኒስም በተለይ በካርል ማርክስና በቭላዲሚር ሌኒን ትምህርት የተመሠረተ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነው።
ማርክሲስም-ሌኒኒስም የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና በመሆኑ፣ በሃይማኖት ፈንታ እንደ የመንግሥት ሃይማኖት ያህል ያለ ሚና አጫውቷል።
በአሁኑ ሰዓት በይፋ የማርክሲስት-ሌኒኒስት መንግሥት ያላቸው አገራት የሚከተሉ ናቸው፦
- ቬትናም - ከ1937 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1982 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «የሆ ቺ ሚን ሃሣብ» ተብሏል።
- የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ - ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1970 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «ሶሻሊስም ከቻይናዊ ጸባይ ጋራ» ተብሏል።
- ኩባ - ከ1951 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።
- ላዎስ - ከ1967 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።
- ስሜን ኮርያ - ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ በይፋ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1964 ዓም ጀምሮ ከማርክሲስም የተደረጀው ርዕዮተ ዓለም «ጁቼ» ኰሙኒስም ተብሏል። በ1983 ዓም ደግሞ «ማርክሲስም» በይፋ ተተወ።
ርስት ሁሉ የመንግሥት መሆኑ እንጂ የግል ርስት አለመኖሩ የሚገኝበት ሁናቴ የጀርመን ፋላስፋ የካርል ማርክስ ፍልስፍና ውጤት ነው። በተጨማሪ ማርክስ የሃይማኖት ወዳጅ ባለመሆኑ መጠን፣ ባለፈው ጊዜ በማርክሲስም-ሌኒኒስም በተገዙት አያሌ አገራት ውስጥ የሃይማኖት ወይም የኅሊና ነጻነት አልተገኘም።
በካርል ማርክስም ፍልስፍና ዘንድ ማንም ሕዝብ እንዳይበልጽጉ መቆጣጠር የመንግሥት ኃላፊነት ነው፣ ስለዚህ «ለሴ ፈር» ከ«ካፒታሊዝም» ጽንሰ ሀሣብ ጋር ይዘመዳል።