የግሪክ አልፋቤት
From Wikipedia, the free encyclopedia
የግሪክ አልፋቤት ቢያንስ ከ800 ዓክልበ. ጀምሮ ግሪክኛን ለመጻፍ ተጠቅሟል። የተደረጀው ከፊንቄ ጽሕፈት ሲሆን የአንዳንዱ ፊደል ጥቅም ከተነባቢ ወደ አናባቢ በመለወጡ የግሪክ አልፋቤት መጀመርያው የአናባቢ ፊደል ጥቅም ያገኘው ጽሕፈት ሆነ። የግሪክ አልፋቤትም በተለይ ለላቲን አልፋቤትና ለቂርሎስ አልፋቤት፣ ለሌሎችም፣ ወላጅ ሆነላቸው። ከግሪክኛ በላይ የግሪኩ ጽሕፈት ለአንዳንድ ሌሎች ልሳናት ተለምዷል።