ባሕር-ዳር
From Wikipedia, the free encyclopedia
ባሕር ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትኾን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሀገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባሕር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማእከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ሕዝብ ከነሱም መኻከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች።