ሐውት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሐ ሑ ሒ ሓ ሔ ሕ ሖ ሗ
ሐውት ወይም በአነጋገር ሐመረ ሐ በአቡጊዳ ተራ ስምንተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች ስምንተኛው ፊደል "ሔት" ይባላል።
በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ሐእ" (ح) ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 8ኛ ነው። "ኀእ" የሚለው አረብኛ ፊደል (ﺥ) ደግሞ ከዚያ ወጣ።
በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (ሐ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ"ኸ" አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ሓ) አንድላይ ነው።
በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከሆይ (ሀ) ከኀርም (ኀ) እና ከኻፍ (ኸ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።